ክሪፕቶ ይገበያዩ
ያለ ስዋፕ ክፍያ
እንደ ቢትኮይን (Bitcoin)፣ ኢቴሪየም (Ethereum) ወይም ላይትኮይን (Litecoin) ያሉ ታዋቂ ዲጂታል ገንዘቦችን ያለ ምንም የሌሊት ማቆያ ክፍያ ያግኙ።

ለምን በ JustMarkets ክሪፕቶ ይገበያያሉ?
ከቀዳሚው ቢትኮይን ጀምሮ እስከ አዲሶቹ ኢቴሪየም እና ላይትኮይን ድረስ፤ JustMarkets በልዩ የገበያ ሁኔታዎች ውስጥ የዋና ዋና የክሪፕቶ ምንዛሬዎችን እንቅስቃሴ ለመከታተልና ለመገበያየት የሚያስችል መድረክ ያቀርብልዎታል።
የተለያዩ የክሪፕቶ ውጤቶች (Derivatives)
ሁልጊዜም በማደግ ላይ ባለው በ JustMarkets የክሪፕቶ ገበያ ውስጥ ይሳተፉ። ንብረቶቹን በቀጥታ መያዝ ሳያስፈልግዎት፤ የዋና ዋና ክሪፕቶከረንሲዎችን የዋጋ መውጣት እና መውረድ አዝማሚያዎች እምቅ አቅም ይጠቀሙ።
ከስዋፕ-ነፃ ንግድ
በ JustMarkets ላይ እያንዳንዱ ነጋዴ ያለምንም ተጨማሪ መስፈርቶች ከስዋፕ-ነፃ የንግድ አገልግሎት ያገኛል፤ ይህም ያለ ተጨማሪ ክፍያ የንግድ ልውውጦችን ለረጅም ጊዜ እንዲያቆዩ ያስችላል።
ፈጣን ወጪ ማድረጊያዎች
ገንዘብዎን ማውጣት ሲፈልጉ በፍጥነት ያግኙ። ከተለያዩ የክፍያ ዘዴዎች ይምረጡ እና ለጥያቄዎችዎ ፈጣን ማረጋገጫ ያግኙ።
የዋጋ መዛባት (Slippage) ጥበቃ
በ ከዋጋ መዛባት (slippage) ጥበቃችን ያለ ምንም ስጋት ይገበያዩ። የዋጋ መዛባቶችን (slippages) ይከላከላል፣ ስለዚህ ምንም አይነት አነስተኛ የዋጋ ለውጦች ሳያመልጡዎት ግብይቶችዎ እርስዎ በጠበቁት ቦታ ይጀምራሉ እንዲሁም ያበቃሉ።
የኢንቨስትመንት ደህንነት
ከእዳ (ከዘሮ በታች ቀሪ ሒሳብ) ጥበቃ ጋር በክሪፕቶ ላይ ኢንቨስት ያድርጉ። በገበያው ላይ በሚፈጠር ፈጣን እንቅስቃሴ ምክንያት ከዜሮ በታች ቀሪ ሂሳብ ሲያጋጥም፣ ደንበኞችን ካልተጠበቀ ኪሳራ ለመጠበቅ ሲባል ሂሳቡ ወደ ዜሮ ይቀየራል።
ፈጣን የትዕዛዝ አፈጻጸም
በ JustMarkets የግብይት ስምምነቶችዎ ወዲያውኑ በሚባል ደረጃ ይፈጸማሉ። በአንድ ሰከንድ ሽርፍራፊዎች ውስጥ ግብይቶችዎ መፈጸማቸውን እናረጋግጣለን ይህም ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመገበያየት የሚፈልጉትን ፍጥነት ይሰጥዎታል።
የክሪፕቶ ገበያ መሣሪያዎች
አማካይ ስፕሬድ
ፒፕስ
ኮሚሽን
በሎት/በአንድ በኩል
ማርጂን
1:3000
ሎንግ ስዋፕ
ነጥቦች
ሾርት ስዋፕ
ነጥቦች
የማቆሚያ ደረጃ (Stop level)
ፒፕስ
Standard
Crypto
የክሪፕቶ ገበያ ሁኔታዎች
ዲጂታል ሳንቲሞችን ለመፍጠር እና ለመለዋወጥ በብሎክቼይን ቴክኖሎጂ ላይ ወደተገነባው ፈጠራዊ የክሪፕቶከረንሲዎች ዓለም ውስጥ ይግቡ። በ JustMarkets መገበያየት የክሪፕቶከረንሲ ዋጋዎች መለዋወጥን ለመከታተል እና መሰረታዊ ንብረቶቹን በባለቤትነት መያዝ ሳያስፈልግዎ የኦንላይን ፖርትፎሊዮዎን በሌቨሬጅ ለማሳደግ ዕድል ይሰጥዎታል።
የንግድ ሰዓታት
በ JustMarkets ከታቀዱ የሰርቨር ጥገና ጊዜያት ውጭ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀናት የክሪፕቶከረንሲ ግብይት ማከናወን ይችላሉ። በኢሜል እና በድረ-ገጻችን ላይ በሚወጡ ዜናዎች አማካኝነት ወቅታዊ መረጃዎችን እናደርስዎታለን።
የሚከተሉት የክሪፕቶከረንሲ ጥንዶች በየቀኑ ከ 00:00 እስከ 00:05 የግብይት ዕረፍት አላቸው፦ BTCUSD፣ BTCEUR፣ BTCGBP፣ BCHUSD፣ ETHUSD፣ LTCUSD፣ XRPUSD።
| መሳሪያ | መክፈቻ | መዝጊያ |
| BTCXAU | ሰኞ 01:02 ከማክሰኞ – አርብ 01:01 |
ከሰኞ – አርብ 23:57 |
| BTCGBP | በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት 7 ቀናት (24/7) ቅዳሜ እረፍት 12:55 – 14:05 |
– |
ሁሉም የጊዜ ሰሌዳዎች በሰርቨር ሰዓት አቆጣጠር (GMT+3) ናቸው።
ስፕሬዶች (Spreads)
በክሪፕቶ ገበያ ውስጥ ስፕሬዶች በተደጋጋሚ ይዋዥቃሉ። ከላይ የተጠቀሱት ስፕሬዶች ካለፉት የግብይት ቀናት የተወሰዱ አማካዮች ናቸው። ወቅታዊ የሆኑ ስፕሬዶችን ለማየት የእኛን ፕላትፎርም ይመልከቱ።
ሊኩዲቲ በሚቀንስበት ወቅት ስፕሬዶች ሊጨምሩ ይችላሉ። ይህ እንደ የገበያ መሸጋገሪያ ያሉ ጊዜያትን የሚያካትት ሲሆን፣ መደበኛ ሁኔታዎች እስኪመለሱ ድረስ ሊቀጥል ይችላል።
ከ 0.0 ፒፕስ በሚጀምሩበት የእኛ ሮው ስፕሬድ አካውንት ላይ ምርጥ ስፕሬዶች ዋስትና ተሰጥቷቸዋል።
ከስዋፕ-ነፃ ንግድ
ስዋፕ ማለት በአዳር ክፍት ሆነው በሚቆዩ የንግድ ፖዚሽኖች (ትዕዛዞች) ላይ የሚታሰብ የወለድ ክፍያ ነው። የስዋፕ መጠኖች በተለያዩ የንግድ ጥንዶች ላይ ይለያያሉ። ፖዚሽኑ እስኪዘጋ ድረስ ስዋፖች ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር በየቀኑ በ 22፡00 GMT+2 ሰዓት ላይ ይተገበራሉ። የየሳምንቱ መጨረሻ (ቅዳሜና የእሁድ) የገንዘብ ወጪዎችን ለማካካስ ሲባል ረቡዕ እለት የሚታሰቡ ስዋፖች በሶስት እጥፍ የሚጨምሩ መሆኑን ልብ ማለት አስፈላጊ ነው።
ከስዋፕ-ነፃ ሁኔታ ካለዎት፣ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ “የተራዘመ ስዋፕ-ነፃ ይገኛል” ተብለው ምልክት በተደረገባቸው መገበያያ መሳሪያዎች ላይ ክፍያ አይጠየቁም።
ከየትኛውም ሀገር ያሉ ሁሉም የደንበኛ አካውንቶች በራስ-ሰር ከስዋፕ-ነፃ ሁኔታ ይሰጣቸዋል።
የማቆሚያ ደረጃ (Stop level)
የማቆሚያ ደረጃ (stop level) ማለት ተጠባባቂ ትዕዛዝን (የኪሳራ ማቆሚያ (Stop Loss)፣ የትርፍ መውሰጃ (Take Profit)፣ መግዛት/መሸጥ ማቆሚያ (Buy/Sell Stop)፣ የመግዛት/መሸጥ ገደብ (Buy/Sell Limit)) በሚያስገቡበት ጊዜ በሚፈለገው የግብይት መክፈቻ ዋጋ እና አሁን ባለው (የገበያ) ዋጋ መካከል ያለው አነስተኛው ተቀባይነት ያለው ርቀት ነው። የማቆሚያ ደረጃው በገበያ ተለዋዋጭነት ጊዜያት የዋጋ መዛባት (slippage) አደጋ ለመቀነስ ይረዳል፣ እንዲሁም ተጠባባቂ ትዕዛዞች ይበልጥ አስተማማኝ በሆነ መንገድ እንዲፈጸሙ ያረጋግጣል።
ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ውስጥ የተመለከቱት የማቆሚያ ደረጃ (stop level) እሴቶች ተለዋዋጭ መሆናቸውን እና የተወሰኑ የከፍተኛ ድግግሞሽ ስልቶችን ለሚተገብሩ ወይም የኤክስፐርት አማካሪዎችን ለሚጠቀሙ ነጋዴዎች ላይገኙ እንደሚችሉ ትኩረት ይስጡ።
ቋሚ የማርጂን መስፈርቶች
የንግድ አካውንትዎ የሚጠቀመው የብድር መጠን (ሌቨሬጅ) ምንም ይሁን ምን፣ ለሁሉም የክሪፕቶከረንሲ ጥንዶች የሚያስፈልገው የዋስትና ማስያዣ (ማርጂን) መጠን ቋሚ ነው።
ሌቨሬጅ
የክሪፕቶከረንሲ ሌቨሬጅ በ 1:20 ቋሚ ሆኖ የተወሰነ ነው፣ ነገር ግን ለአንዳንድ ጥንዶች (pairs) ይለያያል።
የሚከተሉት ክሪፕቶከረንሲዎች ለየት ያሉ ሲሆኑ፣ የሚከተለው ቋሚ ሌቨሬጅ አላቸው፦
| የንግድ መሣሪያዎች | ከፍተኛው ሌቨሬጅ |
| BTCUSD, BTCEUR, BTCGBP, BTCJPY, ETHUSD, BTCXAU | 1:500 |
| BCHUSD, LTCUSD, XRPUSD | 1:200 |
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
1
ክሪፕቶ ምንድን ነው?
ክሪፕቶ፣ የክሪፕቶከረንሲ አጭር መጠሪያ ሲሆን፣ ለደህንነት ሲባል ክሪፕቶግራፊን (ምስጢራዊ ኮድን) የሚጠቀሙ ዲጂታል ወይም ምናባዊ ምንዛሬዎችን ያመለክታል። እነዚህም በብሎክቼይን ቴክኖሎጂ ላይ በተመሰረቱና ማዕከላዊ ቁጥጥር በሌላቸው አውታረ መረቦች (decentralized networks) ላይ ይሰራሉ። ክሪፕቶከረንሲዎች በማንኛውም ማዕከላዊ አካል ቁጥጥር የማይደረግባቸው በመሆናቸው፣ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ወይም ማጭበርበር ነፃ ናቸው።
2
የብሎክቼይን ቴክኖሎጂ ምንድን ነው እና እንዴትስ ይሰራል?
ብሎክቼይን ቴክኖሎጂ በኮምፒውተሮች አውታረ መረቦች ላይ የሚደረጉ ማናቸውንም ግብይቶች የሚመዘግብ ማዕከላዊነት ቁጥጥር የሌለው የሂሳብ መዝገብ ነው። እያንዳንዱ ግብይት እንደ አዲስ ብሎክ ወደ ሰንሰለቱ የሚጨመርና ሊለወጥ የማይችል በመሆኑ ደህንነትን እና ግልጽነትን ያረጋግጣል። ይህ ቴክኖሎጂ ክሪፕቶከረንሲዎች መሰረት ሲሆን፤ ማዕከላዊ አካል ሳያስፈልግ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ማንነትን የማይገልጽ ግብይት እንዲከናወን ያስችላል።
3
ቢትኮይን (Bitcoin) ምንድን ነው?
ቢትኮይን እ.ኤ.አ በ 2009 ሳቶሺ ናካሞቶ በተባለ የብዕር ስም በሚጠቀም ማንነቱ ባልታወቀ ሰው የተፈጠረ ሲሆን፣ የመጀመሪያው እና በጣም የታወቀው ክሪፕቶከረንሲ ነው። ይህ በማዕከላዊ አካል ቁጥጥር የማይደረግ እና ግለሰቦች ያለምንም ጣልቃ ገብ አቻ-ለአቻ (peer-to-peer) ግብይቶችን እንዲፈጽሙ የሚያስችል ዲጂታል ገንዘብ ነው የቢትኮይን (Bitcoin) ግብይቶች አውታረ መረብ ኖዶች (network nodes) በክሪፕቶግራፊ አማካኝነት የሚረጋገጡ ሲሆን፣ ብሎክቼይን በሚባል ይፋዊ የሂሳብ መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ።
4
ምን ዓይነት ክሪፕቶከረንሲዎችን መገበያየት እችላለሁ?
ከሚታወቁት ቢትኮይን (Bitcoin) እና ኢቴሪየም (Ethereum) በተጨማሪ ለንግድ የሚውሉ በርካታ ክሪፕቶከረንሲዎች አሉ። እነዚህም ሪፕል (Ripple) (XRP)፣ ላይትኮይን (Litecoin) (LTC)፣ ካርዳኖ (Cardano) (ADA)፣ ፖልካዶት (Polkadot) (DOT) እና ሌሎችንም ያካትታሉ። ለንግድ የሚቀርቡ የተወሰኑ ክሪፕቶከረንሲዎች መገኘት እርስዎ በሚጠቀሙት ፕላትፎርም ወይም ኤክስቼንጅ ይለያያል።
5
በሌቨሬጅ ክሪፕቶከረንሲን መገበያየት እችላለሁ?
አዎ፣ ብዙ የንግድ ፕላትፎርሞች ለክሪፕቶከረንሲዎች የሌቨሬጅ ንግድ ያቀርባሉ። ሌቨሬጅ የአሁን ካለዎት ካፒታል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲነግዱ ይፈቅድልዎታል፣ ይህም ትርፍዎን ሊያሳድግ ይችላል። ሆኖም ግን ሌቭሬጅ ትርፍን ሊያሳድግ እንደሚችል ሁሉ ከፍተኛ ኪሳራን የማስከተል አደጋንም እንደሚጨምር ማስታወስ አስፈላጊ ነው።
6
በሳምንቱ መጨረሻ (ቅዳሜ እና እሁድ) መገበያየት እችላለሁ?
አዎ፣ ከባህላዊ የአክሲዮን ገበያዎች በተለየ፣ የክሪፕቶከረንሲ ገበያዎች በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት ለ 7 ቀናት ክፍት ስለሆኑ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድ) መገበያየት ያስችላሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት ክሪፕቶከረንሲዎች ማዕከላዊነት የሌላቸው በመሆናቸው እና ከየትኛውም የተወሰነ መልክዓ ምድራዊ ክልል ወይም ማዕከላዊ ተቆጣጣሪ አካል ጋር ያልተያያዙ በመሆናቸው ነው።
